| Format | Paperback |
|---|
መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የስደተኛው መሪ ትረካዎች / Mengistu Hailemariam : Yesidetegnaw Meri Tirekawoch (Afrikaans Edition)
$22.50 Save:$5.00(19%)
Available in stock
| Print length: | 328 pages |
|---|---|
| Language: | Afrikaans |
| Publication date: | September 7, 2024 |
| Dimensions: | 5.83 x 0.83 x 8.27 inches |
| ISBN-10: | 9999054323 |
| ISBN-13: | 978-9999054324 |
People Also Viewed
-
Hooked (Collector's Edition) (Never After, 1)
$25.10
-
Thyroid Transformation Blueprint
$22.45
-
NVI, Santa Biblia, Revisión 2022, Edición económica, Tapa rústica (Spanish Edition)
$2.42
-
Outliers: The Story of Success
$8.77
-
KJV, Pew Bible, Large Print, Hardcover, Black, Red Letter, Comfort Print: Holy Bible, King James Version
$10.16
Description
Mengistu Haile Mariam: Yesidetegnaw Meri Tirekawoch (Narratives of the Exiled Former Leader) offers a rare and intimate glimpse into the life of one of Ethiopia’s most controversial figures, former communist president Mengistu Hailemariam. This autobiographical account, based on exclusive interviews with Mengistu himself, covers aspects of his life never before revealed to the public. Beyond his well-documented political career and the turbulent history of his regime, the book uncovers the human side of a leader often viewed through the lens of power and conflict. Readers will discover the personal struggles, reflections, and experiences that shaped Mengistu’s journey, from his early years to his eventual life in exile. Mengistu Haile Mariam: Yesidetegnaw Meri Tirekawoch sheds new light on the man behind the political persona, offering a compelling, multifaceted portrait of a leader whose legacy still reverberates in Ethiopian history. ………………………………………………………………………………………………………. ከመጽሐፉ የተወሰደ መቼም እናቱን የማይወድ ሰው የለም፣ የእኔ ግን የተለየ ነው፣ እናቴን በጣ. . .ም ነው እወዳት የነበረው፤ እርሷም ትወደኛለች፡፡ ካለእርሷ ሕይወት፣ ሀገርም ሆነ ዓለም አለ ብዬ አላምንም ነበረ፡፡ በዛ የልጅነት ዕድሜዬ እናቴን በሞት ሳጣት ጭንቅላቴ ክፉኛ ነበር በሀዘን የተመታው፤ ክፉኛ ነው ያዘንኩት፤ ተስፋ የቆረጥኩት፡፡ ከዚህ ውጪ የአየር ሃይል ትምህርት ቤት፣ ፖሊስ አባዲና ትምህርት ቤት ከስምንተኛ ነበር የሚቀበሉት፡፡ እነዚህ ነበሩ ያኔ ኢለመንተሪ ትምህርት ጨርሶ ወደከፍተኛ ትምህርት ለሚቀላቀሉ እድል የነበሩት፡፡ ይኼንን ሁሉ ቃኝቻለሁ ያኔ፡፡ በርካቶቹ ሊቀበሉኝ አልቻሉም፤ “በሚቀጥለው ጊዜ ና” አሉኝ፡፡ እዚያ ብቻ አይደለም የሞከርኩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር የዛን ጊዜ ተቋቁሞ ዘፋኝ፣ ዳንሰኛ፣ ምናምን ከሴትም ከወንድም ወጣቶች እየወሰዱ ያሰለጥኑ ነበር፡፡ ከተቻለ በወቅቱ የነበረው አንዱ ዕድል እሱ ነበርና እዚያም ሔጄ ተመዝግቤያለሁ፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት የሰውነቴ መጠን የዕድሜዬን ደረጃ አልፈቀደም፡፡ ወዲያ ወዲህ ብል ግራ ገባኝ፡፡ ህጻናት አምባ የእኔ ፈጠራ ነው፤ ህጻናት አምባን ለመፍጠር ያስገደደን የሀገራች የወቅቱ ሁኔታ ነው፡፡ ህጻናት አምባን እንደ ቤቴና ልጆቹን እንደልጆቼ ከልቤ ነው የማየው፡፡ ምክንያቱም እናት አባት የሌላቸው ናቸው፤ እናት አባት ማን ሊሆን ይችላል? እነሱን የቀረባቸውና እንደ ወላጅ የሚያያቸው እሚያዝንላቸው ስለነሱ ኋላፊነት የሚወስድ ማን ሊሆን ይችላል? ጉዳዩ ፖለቲካዊ አይደለም፤ ልባዊ ነው፡፡ ልጆቹን ከልቤ እንደልጆቼ ነው የማየው፡፡ በአንድ ወቅት ሁላችሁም እንደምታስታውሱት ጥላሁን ገሰሰ በእግሩ ላይ ባጋጠመው የጤና እክል ደቡብ አፍሪካ ህክምና አድርጎ ነበር፡፡ ወንዱ ልጄ አንድነት ፈልጎ ፈላልጎ የሆስፒታሉን አድራሻ አገኘው፡፡ በጊዜው ባጋጠመው ነገር የተሰማኝን ሃዘን ለመግለጽ ስልክ ደወልኩለት፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከአሜሪካን ሀገር አብረው ይምጡ፣ ወይም ደግሞ ሊጠይቁት በዛን ቀን እዚያ ይገኙ ባላውቅም ዓለምፀሀይ ወዳጆና ንዋይም አብረውት ነበሩ፡፡ ሰውዬው የዚሁ የዚምባቡዌ ሀገር ሰው ነው፡፡ ሲታይ ያሳዝናል፣ የተጎሳቆለ ነው፡፡ ገንዘብ ለዚህ ካልሆነ እያልኩ የተወሰነ ጊዜም መጽውቼዋለሁ፡፡ ውቤም ልብስ ምናምን ሰጥታው ታውቃለች፡፡ . . . አንድ ሰው እዚህ ስፍራ ላይ አስቀምጠው አስጠንተዋል ለካ፡፡ ይህ ከእጃችን የመጸወትነው፣ ከቤታችን ልብሳችንን አውጥተን የሰጠነው ምስኪን መሳይ ሰው በኤምባሲው አማካኝነት የተቀጠረ የወያኔና ሸዕቢያ መረጃ አቀባይ ነበር፡፡ የማያስደስት ታሪክ . . . በአንደዳንድ መልኩም የሚያስለቅስም ነው፡፡ “የትላንቱ ግድ የለም ለሀገር ተብሎ ይኼ ሁሉ ተከፍሏል፤ ነገ ምንድነው ተስፋችን?” ብዬ ስጠይቅ ተስፋ አይታየኝም፡፡ ምንአልባት ተሳስቼ ሊሆን ይችላል፡፡ “ኢትዮጵያ ሊመጣባት የሚችለውን ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ችግር የሚቋቋም ማዕከላዊ ፎርስ ማን ነው? ለአንድነቷ፣ ለሰላሟ” ብዬ ስጠይቅ መልስ የለኝም፡፡ ይኼው ነው! ………………………………. የደራሲው ቀደምት ስራዎች:- ጥቁር ነጥብ 1993 (የግጥም ስብስብ) ደጅ ያደረ ልብ 1997 (የግጥም ስብስብ) የደመና መንገድ 2007 (የአጭር ልብወለዶች ስብስብ) — ASIN: 9999054323 | ISBN13: 9789999054324 | ISBN-13: 978-9999054324
Reviews (0)
Only logged in customers who have purchased this product may leave a review.












Reviews
There are no reviews yet.